ዳማ ከሴ (Ocimum sauve Willd(Labiatae) ) በኢትዮጵያ የሚበቅል ዕፅ ሲሆን እንደ ከሴ (ስ. ጥሩ ሽታ ያለው የቁጥቋጦ አይነት። ዕቃ ማጠኛ[1] ወይም ኮሰረት Lippia adoensis (Verbenaceae) ያለ ለመድኅኒትነት የሚጠቀሙበት ነው።
ይሄ ዕጽ በሺ ስድስት መቶ እስከ ሁለት ሺ ሁለት መቶ ሜትር ከፍታ ባሉ ሥፍራዎች የሚበቅል ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ለመድኅኒትነት ጥቅም የሚውለው ቅጠሉን በመጭመቅና በማሽተት፣ ወይም ቅጠሉን በውሐ አፍልቶ በመታጠን ወይም በመጠጣት ነው።[2]
ለጉንፋን፣ ለራስ ምታትና ለውሻ ልክፍት (በተለምዶ - ያድን አያድን አይታወቅም) ይጠቀማል።
የቅጠሉ ጭማቂ በውሃ ወይም በቡና ለትኩሳት («ምች») ይሰጣል።[3][4]
የቅጠሉ ወይም የልጡ ለጥፍ በቁስል ይለጠፋል።[5]
MEDICINAL PLANTS"፣ August 2003
ዳማ ከሴ (Ocimum sauve Willd(Labiatae) ) በኢትዮጵያ የሚበቅል ዕፅ ሲሆን እንደ ከሴ (ስ. ጥሩ ሽታ ያለው የቁጥቋጦ አይነት። ዕቃ ማጠኛ ወይም ኮሰረት Lippia adoensis (Verbenaceae) ያለ ለመድኅኒትነት የሚጠቀሙበት ነው።
ይሄ ዕጽ በሺ ስድስት መቶ እስከ ሁለት ሺ ሁለት መቶ ሜትር ከፍታ ባሉ ሥፍራዎች የሚበቅል ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ለመድኅኒትነት ጥቅም የሚውለው ቅጠሉን በመጭመቅና በማሽተት፣ ወይም ቅጠሉን በውሐ አፍልቶ በመታጠን ወይም በመጠጣት ነው።