መቅመቆ (Rumex abyssinicus) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
የእርሻም ሆነ የውድማ አረም ነው።
ድንቼው ቀይ ንክር ቀለም ይሠራል፣ የሴቶች እጅና እግር ለማጌጥ ነው። ድንቼው ሲበሠል ጠንካራ ቢጫ ንክር ቀለም ይሠራል፣ ይህም ለቅቤና ለቅመም ነው።[1]
በባሕል መድሃኒት፣ ሥሩ በቋቁቻ ላይ በቀጥታ ይቀባል። ሥሩም ተደቅቆ በውሃ ተፈልቶ ለደም ብዛት ለማከም ይጠጣል።[2] ሥሩም ለደም ብዛት ወይም ለጉሮሮ ብግነት ይኘካል። ሥሩ ተደቅቆ በወተትና ቅቤ ለእንቅርትና ለአሚባ በሽታ ይጠጣል።[3]