ኣበቃ ወይም ምስርች (Rotheca myricoides) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
ብዙ ጊዘ ከአንድ ሜትር በላይ ይደርሳል፣ ሰማያዊ፣ ወይን ጠጅ ወይም ነጭ አበቦች አሉት።
በቆዩ መኖርያ ቤቶችና በተፈጁ ኮረብቶች በጣም ተራ ነው።
በመጀመርያ ከአፍሪካ ሲሆን በሌላ አገር እንደ አበባ ይታደጋል።
ሥሮቹን በማፍላት የተሠራው መረቅ መርዝን የሚሽር መድኃኒት በመሆን ይጠጣል።
እንዲሁም ተክሉ ትልን ለመግደል፣ በከብትም ለሚያስቀምጥ መድኃኒት ተጠቅሞዋል። የተክሉ መረቅ ደግሞ ለቁስል ፋሻ ይጠቀማል።
ከብሳና ቡቃያና ከእምቧይ ሥር ጋራ ተቀላቅሎ፣ የሆድ ድርቀት ለማከም በአፍ ይወሰዳል። ቅቤም ለለጥፉ ይጨመራል።[1]
በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ እንደ ተዘገበ፣ «አልማዝ ባለጭራ የሚባል ልክፈት ለማከም የምስርች ቅጠል ተድቅቆ በውሃ ይለጠፋል።[2]
በፍቼ ወረዳ እንደ ተዘገበ፣ የምስርች ሥር ጭማቂ በውሃ ለማስታወክ ይጠጣል።[3]