እምቧጮ (Rumex nervosus) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
እስከ 2 ሜትር የሚደርስ ቊጥቋጥ፣ ብዙ አገዶች ከመሬት ይነሣሉ፣ ልጡ ቡላማ፣ ቅጠሎች ትንሽ ውሃማ ናቸው።
ድካም ደረቅ አፈር ይመርጣል።
በማናቸውም ከፍታ ይገኛል፣ በመንገድ ዳር፣ በተፈጀ መስክ። በድሬ ዳዋ አካባቢ ያለው ደንገጎ ተራራ ከዚህ ተክል ኦሮምኛ ስም (ደንገጎ) ነው።
ቅጠሉ አገዳውም በሰፊ ጫትን ለመጠቅለል ይጠቀማል። ወፍራም፣ ውሃማው ቅጠሎች ጫትን ለረጅም ጊዜ ይጠብቃሉ።
ውሃማው ቡቃያ በእረኞች ይበላል። ቡቃያው ቶሎ፣ ለኣጭር ጊዜ፣ በእሳት ውስጥ ቢሳክ፣ ለስላሳ ይሆናልና በልጆች ይወደዳል።
የአገዳው ከሰል ከእንቁላል አስቋል ተቀላቅሎ የቆዳ መቃጠል ለማከም ይጠቀማል። ቅቤም ይጨመራል። [1]
የእምቧጮ ቅጠልና አገዳ በሎሚ ጭማቂና ውሃ ተደቅቆ ለብጉርና ለእከክ ይቀባል።[2]
የእንቧጮ ሥር ዱቄት በኪንታሮት በተቈረጠው ጫፍ ላይ ለማከም ይደረጋል። የሥሩም ዱቄት ከተቀለጠ ቅቤ ጋር ለተቅማጥ ይጠጣል። ሥሩም በማር ለጥፍ ለሆድ ቁርጠት ይበላል።[3]